Posts

Showing posts from June, 2024

አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡9-10

Image
  ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡9-10 ፩. ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፡፡ በምድር ላይ ታዋቂ ላንሆን አንችላለን፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ ግን ታዋቂዎች ነን፡፡ እግዚአብሄር ልኮናል ፣ እግዚአብሄር ያውቀናል ፣ እግዚአብሄር ተደስቶብናል፡፡ ሰው እንደሚያይ የማያየው እግዚአብሄር ያውቀናል፡፡ ሰው የናቀውን የሚያከብር እግዚአብሄር ዋጋ ሰጥቶናል፡፡ ጉዳዬ ልንለው የሚገባው የእግዚአብሄርን እይታ ብቻ ነው፡፡ በሰው ዘንድ ለመታወቅ ጉልበታችን አንጨርስም፡፡ ለጠራን ለመሮጥ እንጂ ለታዋቂነት ለመፍጨርጨር ትርፍ ጊዜ የለንም፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን እንድንፈፅመው የጠራንን ጥሪ በዝምታ እንፈፅማለን፡፡ ሰው እንደ እግዚአብሄር አያውቀንም የሰው ማክበርን ማዋረድም አያስደንቀንም፡፡ በሰው ዘንድ ያልታወቅን ስንባል የታወቅን ነን፡፡ ሰውንም ለማስደሰት በምድር ላይ የለንም፡፡ ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና። ዮሃንስ 12፡43 ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም። ገላትያ 1፡10 ፪. የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፡፡ የምንሰራው ምድራዊ እና ስጋዊ ነገር አይደለም፡፡ የምንኖረው ፣ የምንወጣውና የምንገባው በራሳችን ጉልበት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር እርዳታ በሃይል ከእኛ ጋር አለ፡፡ እንድንኖርለትና እንድናገለግለው የጠራን በሃይል ከእኛ ጋር ይሰራል፡፡ ምንም በጎ ነገር ቢገኝብን ከእርሱ ነው፡፡ በራሳችን ስንደክም እንኳን የእርሱ...